ዋሺንግተን ዲሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
የዓለም ባንክ ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ጉዳይ ቅድሚያ እንዲሰጥና ተጠያቂነትም እንዲኖረው ያሳሰቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ የሆኑ እንዲሁም የሌሎችም ሃገሮች ሰልፈኞች ከትናንት በስተያ ቅዳሜ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የባንክና የዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም - አይኤምኤፍ ጠቅላይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት የተቃውሞ ጥሪ አሰምተዋል፡፡
ሰልፈኞቹ የዓለም ባንክ ለሰብዓዊ መብቶችና ለተፈጥሮ ጥበቃ ቅድሚያ እንዲሰጥ፣ አምባገነን መንግሥታትን እንዳይረዳ፣ መፈናቀልና የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችን የሚፈፅሙ ፕሮጀክቶችን እንዳይደግፍ ጠይቀው ፅህፈት ቤቱን እየዞሩ መፈክሮቻቸውን አሰምተዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡