በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚመለከት ልዩ ችሎት በትግራይ እንዲቋቋም ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን የሚመለከት ልዩ ችሎት በትግራይ እንዲቋቋም ተጠየቀ

በትግራይ ክልል በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና የግድያ ወንጀሎችን የሚመለከት ልዩ ችሎት እንዲቋቋም የተጎጂ ቤተሰቦች ጠየቁ።

ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ተጎጂ ቤተሰቦች፣ በሴቶች ላይ ይፈጸማሉ ላሏቸው ጥቃቶች አስቸኳይና ተመጣጣኝ ፍትህ እንደማይሰጥ ተናግረዋል።

በሴቶች ጥቃት መካከል የሚሰራ “ይኾኖ” የተባለ የሲቪል ማኅበረሰብ ተቋም በበኩሉ፣ በክልሉ የሚታየው በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች የሚቆሙት ሁሉም ኅበረተሰብ በጋራ ተቃውሞ ሲያሰማ ነው ብለዋል።

የትግራይ ሴቶች ማኅበር ባወጣው ሪፖርት በበኩሉ፣ "በአንድ ዓመት ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉ 44 ሴቶች 24ቱ በባሎቻቸው የተገደሉ ናቸው" ብሏል።

የክልሉ ፍትሕ ቢሮ በጉዳዩ ላይ በሰጠው ምላሽ፣ ጦርነቱ በክልሉ የፍትሕ ተቋማት ላይ ያደረሰው የሰው እና የንብረት ጉዳት ከፍተኛ በመኾኑ በሴቶች ጥቃት እልባት ለመስጠት መዘግየትን እንደምክንያት አስቀምጧል።