የሟቾቹ የቀብር ሥነ ሥርዓት አንዱ በወልዲያ አንዱ ደግሞ በማይጨው መፈፀሙ ታውቋል። ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች መቁሰላቸውና ከ200 ሰው በላይ የንብረት ውድመት እንዳጋጠመው የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የመቀሌና የወልዲያ ከተማ የእግር ኳስ ከለቦች እሁድ ዕለት ሊያደርጉት ለነበረው የጨዋታ ውድድር ከጨዋታው በፊት የተፈጠረው ግጭት ወደ ብሔር ግጭት ተለውጦ እንደነበርና በዚህም ከሁለቱም ወገን የሁለት ሰው ሕይወት መጥፋቱን ነዋሪዎችና የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።
በተጨማሪም ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን የትግራይ ተወላጆች ሆቴልና ድርጅት መሰበሩን፣ መኪና መቃጠሉና በአጠቃላይ ወደ 200 መቶ የሚጠጉ ድርጅቶች ላይ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5