ሀዋሳ —
“ከህወሓትና ከኦነግ ጋር ተመሳጥረው ሃገር ለማፍረስ እየሠሩ ናቸው” ያላቸውን የወላይታ ዞን አመራር አባላትን ጨምሮ ሃያ ስድስት ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።
ይህንን ተከትሎ በዞኑ ዋና ከተማ ሶዶና ቦዲቲ ከተማ ውስጥ ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ህይወት መጥፋቱን የዐይን እማኝ ነን ያሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
አካባቢውን የመከላከያ ሠራዊት መቆጣጠሩን ነዋሪዎች ገልፀው ሃገር አቋራጩን አውራ ጎዳና ጨምሮ ወላይታ ሶዶን ከሰባት አከባቢዎች ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ትናንት ማምሻውን ጀምሮ መዘጋታቸውን ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5