በምሥራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ያለው ሁከት የኢቦላ በሽታ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የተያዘውን ጥረት እያደናቀፈ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
በምሥራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፖብሊክ ያለው ሁከት የኢቦላ በሽታ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የተያዘውን ጥረት እያደናቀፈ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
ኢቦላ እስካሁን በአካባቢው ከአንድ መቶ ሃምሳ በላይ ሰዎች ገድሏል። የዓለም የጤና ድርጅቱ ቃል አቀባይ ታሪክ ዣሳሬቪች በሰጡት ቃል በጣም ከባድ ሁኔታ ነው ይሄ ከመጀመሪያው አንስተን የፈራነው ነገር ነው የፀጥታ ሁኔታው ሙሉ በሙሉ ሥራችንን ለማከናወን የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።
በኮንጎ ሰሜናዊ ኪቩ ክፍለ ሃገር የኢቦላ ወረርሽኝ የተቀሰቀሰው ብዛት ያላቸው ታጣቂ ቡድኖች የሚንቀሳቀሱበት ሲሆን የዕርዳት ሰራተኞች ወርሽኙ ከጀመረበት ከሃምሌ ወር ወዲህ በተደጋጋሚ ሥራቸውን እንዲያቆሙ ወይም ዝግ እንዲያደርጉ ሲገደዱ ቆይተዋል፡፡