የዓለም ጤና ድርጅት ለወባ በሽታ መከላከያ የሚኾን ዐዲስ አማራጭ ክትባት ለሕጻናት እንዲሰጥ ፈቀደ።
በእንግሊዝ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የበለጸገው R21/Matrix M የተሰኘው ክትባት፣ በህንድ ሴረም ተቋም የተመረተ ሲሆን፣ በቡርኪና ፋሶ፣ ጋና እና ናይጄሪያ ጥቅም ላይ እንዲውል የዓለም ጤና ድርጅቱ ፈቅዷል።
በወባ በሽታ ላይ ምርምር በማደርግበት ወቅት ውጤታማ ክትባት እንዲኖር አልም ነበር፣ አሁን ሁለት ክትባቶች አሉን”
“በወባ በሽታ ላይ ምርምር በማደርግበት ወቅት ውጤታማ ክትባት እንዲኖር አልም ነበር፣ አሁን ሁለት ክትባቶች አሉን” ብለዋል የጤና ድርጅቱ ሓላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም።
ከሁለት ዓመታት በፊት በእንግሊዝ በሚገኝ የመድሃኒት ኩባንያ የበለጸገው RTS, S የተሰኘው ክትባት፣ የጤና ድርጅቱ ሕጻናትን ከወባ ለመከላከል እንዲውል የፈቀደው የመጀመሪያው ክትባት ነው።
“ሁለቱ ክትባቶች በአፍሪካ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ወጣቶችን ሕይወት ያድናል” ሲሉ በአፍሪካ የጤና ድርጅቱ ሓላፊ ማታሺዲሶ ሞኤቲ ተናግረዋል።