ኮቪድ-19 በአፍሪካ - የዓለም የጤና ድርጅት ሪፖርት

  • ቪኦኤ ዜና

የዓለም የጤና ድርጅት ባወጣው አዲስ ሪፖርት አፍሪካ ውስጥ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ካልተገታ 44ሚሊዮን ህዝብ በቫይረሱ ሊጠቃ እንደሚችል፣ 190ሺህ ሰዎች ለህልፈት ሊዳረጉ እንደሚችሉ አሳሰበ።

47 የአፍሪካ ሃገሮችን የዳሰሰው ይህ ሪፖርት፣ በዓለምቀፉ ወርርሽኝ የመጀመሪያው ዓመት ላይ አፍሪካ ውስጥ የሚታየው የቫይረሱ ስርጭት ከተቀረው አካባቢ ጋር በንጽጽር ቀስ ያለ ቢሆንም፣ ስርጭቱ አብዝቶ የሚፀናባቸው ብሎ በገለፃቸው አካባቢዎች ኮቪድ -19 ለረጅም ጊዜ በከበደ መልኩ መቀጣጠሉ እንደማይቀር አስረድቷል።

የዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶ/ር ማትዢሲዶ ሞቲ ምርመራ ማካሂድ ፣ ከህሙማን ጋር የተገናኙ ሰዎችን ተከታትሎ ማግኘት፤ ለይቶ ማቆየትና ማከም አስፈላጊነቱን አስገንዝበዋል።