ኢሚግሬሽንን በተመለከተ ዋይት ኃውስ ትናንት አንድ አስታራቂ ሃሳብ ለምክር ቤት አባላት ማቅረቡ ተገለፀ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
ኢሚግሬሽንን በተመለከተ ዋይት ኃውስ ትናንት አንድ አስታራቂ ሃሳብ ለምክር ቤት አባላት ማቅረቡ ተገለፀ።
ለምክር ቤቱ አባላት የቀረበው ይህ አስታራቂ ሃሳብ፣ ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መጥተው በጥገኛነት ለሚኖሩና “ድሪመርስ” በመባል ለሚታወቁ 1.8 ሚሊዮን ሕፃናት፣ ከአንዳንድ ቅድመ ሁኔታ ጋር፣ ዜግነት የማግኘት ዕድል እንዳለውም ታውቋል።
በዳካ ፕሮግራም አማካኝነት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ እንዲኖሩ የተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎችና እንደ ሥራ፣ ትምህርትና ጥሩ ሥነምግባር የመሳሰሉትን መስፈርቶች ጨምሮ፣ ከ10 - 12 ዓመት ባለው ጊዜ የዜግነት ጥያቄ ማቅረብ እንደሚቻልም ተመልክቷል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ይህን ያቀረቡትን ሃሳብ በተመለከተ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በሰጡት ፍንጭ፣ እነዚህ 1.8 ሚሊዮን ሕፃናት ሊጨነቁ እንደማይገባቸው ገልጸዋል።