የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ለኮቪድ-19 ተጋለጡ

  • ቪኦኤ ዜና
ፎቶ ፋይል፦ የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ

ፎቶ ፋይል፦ የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ኮቪድ-19 ቫይረስ የተጋለጡ መሆኑን ትናንት እሁድ አስታውቀዋል፡፡

ቃል አቀባይዋ፣ ከፕሬዚዳንቱ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ባለፈው ማክሰኞ መሆኑን ገልጸው፣ ማስክ አድርገውና ከሁለት ሜትር በላይ ተራርቀው እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

አሶሼይትድ ፕሬስ እንደዘገበው ባይደን ባለፈው ቅድሜ ተመርምረው ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡