2መቶ ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች ሶሪያ ይቆያሉ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል

ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችዋን ከሶሪያ ካስወጣች በኋላ ቢያንስ ሁለት መቶ የሚሆኑ ወታደሮቿ እንደሚቆዩ ትናንት ዋይት ሃውስ አስታውቋል።

የዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት ቃል አቀባይ ሳራ ሳንደርስ በሰጡት መግለጫ “ጥቂት ሰላም አስከባሪዎች ይቆያሉ” ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ሶሪያ ውስጥ የእስልምና መንግሥት ርዝራዥ ታጣቂዎችን የሚወጉትን የኩርድ ኃይሎች የሚረዱ ወደ ሁለት ሺህ የሚጠጉ አሜሪካውያን ወታደሮች አሉ።