"ጋሽ ተስፋዬ በጣም ብዙ ሰው ነው። በጣም በማይበርድ የቲያትር ፍቅሩ ነው የማስታውሰው። ከ60ዓመታት በላይ በጥበብ ህይወት ውስጥ ኖሯል።”ጌትነት እንየው።“ከሃረር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መጥቼ የቲያትር ዲፓርትመንት መኖሩን እንኳን አላውቅም ነበር። ጂግራፊ ወይ ሌላ ትምህርት ለመማር ነበር አስብ የነበረው። በሶስተኛ ዓመት ተማሪዎች የቀረበ የጋሽ ተስፋዬ ድርሰት ባህል ማዕከል ይታይ ነበር። ከዚያ የተለጠፈ ፖስተር ነው ቲያትር ለመማር ምክኒያት የሆነኝ"ዓለማየሁ ታደሰ።
ዋሽንግተን ዲሲ - አዲስ ኣበባ —
ከሃምሳ በላይ ዓመታት በመምህርነት አገልግሏል። ራሳቸው የቅርስ ያህል ከገዘፉ እና ለሃገር መሠረት ዘለቄታ እና ፋይዳ ባለው የጥበብና የታሪክ ቅርስ ቅብብሎሽ ሂደት ውስጥ እስከ መጨረሻው ሳይታክቱ ሲሰሩ ከቆዩ ጥቂት አንጋፋ ከያንያንም አንዱ ነበር። በሰማኒያ አራት ዓመቱ በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ዘርፈ-ብዙ ከያኒ ተስፋዬ ገሰሰ።
ለወዳጆቹና ለአድናቂዎቹ ብቻ ሳይሆን በተለየ መንገድ ለብዙዎች ቅርብ መሆን ያስቻለው ተፈጥሮ የተቸረም ይመስላል። ህይወት እና ሥራውን ለመዘከር ለተሰናዳ ወግ ሶስት የሞያ ልጆቹ ተገኝተዋል።
እነርሱም በራሳቸው መንገድ ከፍተኛ ዕውቅና ያላቸው ዘርፈ-ብዙ የመድረክ ሰዎች ናቸው። ጌትነት እንየው እና ዓለማየሁ ታደሰ ከአዲስ አበባ፤ ዓለማየሁ ገብረ-ህይወት ደግሞ ከዚህ ከዩናይትድ ስቴትስ ከቨርጂኒያ ክፍለ ግዛት ነው። ለየት ያለ አድናቆትና አክብሮት ሥለ ተሰጠው መምህርና የሞያ አባታቸው ያወጉናል።
Your browser doesn’t support HTML5