ዓለም ትኩረቱን ሁሉ ባለፈው ሣምንት ወደተጠቃችውፓሪስ ያዙር እንጂ ሽብር ፈጠራ በብዙ የአፍሪካ ከተሞችውስጥ የበረታ ሥጋት እንደሆነ መቀጠሉ እየተነገረ ነው።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በዚህ ሣምንት ውስጥ በፅንፈኛው የሁከት ቡድን በቦኮሃራም የተካሄደ ነው የተባሉና የብዙ ሰው ሕይወት ያጠፉጥቃቶች በተለያዩ የናይጀሪያ ከተሞች ላይ ተፈፅመዋል።
ታጣቂዎቹን የፈሩ በብዙ አካባቢዎች ያሉ ሰላማዊነዋሪዎች ቤትና መንደሮቻቸውን እየጣሉ እየተሰደዱነው።
ትናንት፤ ረቡዕ፣ ኅዳር 8/2008 ዓ.ም ዋሺንግተን ዲሲ ላይየተገናኙት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃንኬሪ እና የአንጎላ አቻቸው ዦርዥ ሺካውት በልዩ ሁኔታአተኩረው የተወያዩት በአፍሪካ የፀጥታ ጉዳይ ላይ ነበር።
ቡሩንዲ ውስጥ ሁከት እየተቀጣጠለ መሆኑንና መፍትኄለማግኘት አንጎላ ቁልፍ ሚና እየተጫወተች መሆኗን ኬሪአስታውቀዋል።
ካለፈው ሚያዝያ አንስቶ ፕሬዚዳንት ፒየር ንኩሩንዚዛየሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌ በሚረግጥ ሁኔታ ለሦስተኛየሥልጣን ዘመን ከተወዳደሩ ወዲህ ቡሩንዲ ሁከትእያረገዘች መሆኗ እየተነገረ ነው።
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ያፈነገጡና የሸፈቱ የየጎሣውታጣቂዎች ሰላማዊውን ሰው እያመሱት ነው እየተባለነው።
ናይጀሪያ ውስጥ ካኖና ዮላ ከተሞች ውስጥ በዚህ ሣምንትየደረሱትና የሰላሣ በላይ ሰው ሕይወት ያጠፉትፍንዳታዎች ቦኮ ሃራም ገና አለመንበርከኩን እያሳዩመሆናቸው እየተነገረ ነው።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5