በግጭት ለተፈናቀሉ ድጋፍ ቀረበ

Your browser doesn’t support HTML5

በግጭት ለተፈናቀሉ ድጋፍ ቀረበ

በአፋር እና በአማራ ክልሎች በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች የሚያደርገውን የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ ማጠናቀቁን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ፣ በሁለቱ ክልሎች 300 ሺሕ ለሚሆኑ ሰዎች የምግብ ድጋፍ ማቅረቡን ነው የገለጸው፡፡

በትግራይ ክልል ደግሞ ከግንቦት ወር ወዲህ ከ2.4 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ድጋፍ ቢደርሳቸውም በእንቅስቃሴ ገደቦች ምክንያት የድጋፍ አቅርቦቱ ወደኋላ መቅረቱን አስታውቋል፡፡