የምዕራብ ኦሮምያ አለመረጋጋት የኅብረተሰቡን ኑሮ አስቸጋሪ ማድረጉ ተገለፀ

በምዕራብ ኦሮምያ በሚስተዋለው የፀጥታ ችግር ተማረው ወደ ጋምቤላና ሌሎችም ከተሞች እየሸሹ እንደሆነ አንዳንድ የቄለም ወለጋ ነዋሪዎች ተናገሩ።

በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎችና ራሳቸውን የነፃነት ተዋጊዎች ነን ብለው በሚጠሩ ሸማቂዎች መካከል የሚደረገው ተኩስ ልውውጥ ህይወታቸው ላይ አደጋ መጋረጡንም አነዚህ ነዋሪዎች ገልፀዋል::

የወለጋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ሰብዓዊ መብት መምህራን የምዕራብ ኦሮምያ አለመረጋጋት የኅብረተሰቡን ኑሮ አስቸጋሪ ማድረጉን ተናግረው ለኅብረተሰቡ ሰላም ሲባል ሁለቱም አካላት ያሉበትን መንገድ ቆም ብለው ማጤን እንዳለባቸው አሳስበዋል::

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የምዕራብ ኦሮምያ አለመረጋጋት የኅብረተሰቡን ኑሮ አስቸጋሪ ማድረጉ ተገለፀ