አምቦ —
በምዕራብ ኦሮምያ አንዳንድ ዞኖችና ከተሞች የትራንስፖርትና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች ለቪኦኤ ተናግረዋል።
በሌላ ኩል "ኦነግ ሸኔ" የሚባሉ ታጣቂዎች በምዕራብ ኦሮምያ አንዳንድ ቦታዎች መንገድ ለመዝጋት ጥረት አድርገዋል ያለው የኦሮምያ ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ የተዘጋ መንገድ እንደሌለ ገልጿል።
የኦሮምያ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤትም በበኩሉ ራሳቸውን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” በሚሉ የሚጠሩ መንግሥት ደግሞ "ሽኔ" የሚላቸው ታጣቂዎች “ኦሮምያ ውስጥ የያዙት ቦታ የለም፤ አንዳንዴ ግን መንገድ ለመዝጋት ሙከራዎችን ያደርጋሉ" ብሏል።
በሌላ በኩል በአራቱ ወለጋ ዞኖች አብዛኛው ስፍራ ላይ የኢንተርኔት አገልግሎት ካለፈው ዓርብ ጀምሮ መቋረጡን ያረጋገጡት የኢትዮ-ቴሌኮም የምዕራብ ሪጅን ሥራ አስኪያጅ ችግሩ የተፈጠረው በቴክኒክ እክል ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5