አምቦ —
ከቤኒሻንጉል ጉምዝ አሶሳ ዞንና ካማሽ ተፈናቅለው በኦሮምያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን መነ-ሲቡ ወረዳ ውስጥ መጠለላቸውን የሚናገሩ ሰዎች በቂ ድጋፍ አለማግኘታቸውንና ለችግር መጋለጣቸውን አስታውቀዋል።
የኦሮምያ ክልል አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉትን በመርዳት ላይ እንደሚገኝ አመልክቶ ምዕራብ ወለጋ ያሉ ተፈናቃዮችንም መረጃው ተጠናቅሮ እንደደረሰን ድጋፍ እናደርጋለን ሲል ለቪኦኤ ገልጿል።
በተያያዘ ዜና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽንም በክልሉ ውስጥ ከ361 ሺ በላይ ተፈናቃዮች መኖራቸውን ጠቅሶ በአጠቃላይ ከ417 ሺ በላይ ለችግር የተጋለጡ ሰዎችን በመደገፍ ላይ እገኛለሁ ብሏል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5