Your browser doesn’t support HTML5
በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን፣ በሚገኙት ቤጊ እና ባቦ ገምበል ወረዳዎች፣ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎችና እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካካል በቀጠለው ግጭት መሃል ሰላማዊ ሰዎች ኢላማ እየተደረጉ ነው ሲሉ ነዋሪዎች በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።
የመንግሥትም ሆነ የአማጺው ቡድን ታጣቂዎች መሳሪያ ይዘው ስለሚንቀሳቀሱ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ ባለፈው አርብ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ/ም.ሁለት
ሰላማዊ ሰዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተገድለዋል ሲሉ ከሰዋል።
አምስት ሰዎች ደግሞ፣ “ልጆቻችሁ ወይም ባለቤቶቻችሁ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ናቸው” በሚል በተመሳሳይ ቀን በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ታስረዋል ሲሉ እነዚሁ ነዋሪዎች አቤቱታ አቅርበዋል።
ነዋሪዎቹ ባነሱት ቅሬታ ላይ ከቤጊ እና ባቦ ገምበል አስተደዳር ምላሽ ለማግኝነት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
ነገር ግን የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳር አቶ ሰለሞን ታምሩ ለአሜሪካ ድምፅ በጽሁፍ በሰጡት ምላሽ “የዞኑ የፀጥታ ሁኔታ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ተሻሽሏል” ሲሉ ገልፀዋል።