የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት መጀመር አስመልክቶ አስተያየት

በምእራብ ኦሮምያ ወለጋ ዞኖች ተዘግቶ የነበረው የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት መከፈቱ እንዳስደሰታቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው።

አገልግሎቱ እንዲቋረጥ የተደረገው “በፀጥታ ችግር” ምክንያት እንደነበረ የምዕራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ ጠቅሰው አሁን መከፈቱ ኅብረተሰቡ የኮሮናቫይረስን ሥርጭት መከላከል እንዲችል ለማድረግ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

አገልግሎቱን “ለእኩይ አድራጎት ይጠቀማሉ” ያሏቸው ግለሰቦችም ያንን አድራጎታቸውን እንዲያቆሙና ለበጎ ተግባር እንዲያውሉት አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል::

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የስልክና ኢንተርኔት አገልግሎት መጀመር አስመልክቶ አስተያየት