Your browser doesn’t support HTML5
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጉባ ቆርቻ እና ሻናን ዱንጎ ወረዳዎች ትላንት ማክሰኞ መስከረም 28 በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሣ በተከሠተው የመሬት መናድ፣ 10 ሰዎች መሞታቸውን የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች አስታወቁ።
የጉባ ቆርቻ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መልካሙ ኤርቤሎ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ/ም በጃርጃታ ቀበሌ ውስጥ በተከሰተው የመሬት መናድ ምክንያት አራት ሰዎች ሲሞቱ፣ በሌላ ቀበሌ በደረሰው አደጋ ደግሞ አንድ ሰው ሞቷል።
በሻናን ዱንጎ ወረዳ በሌሊስቱ ቀበሌ በዚሁ ቀን በተከሰተው ሌላ የመሬት መናድ አደጋ የአምስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አደም አባስ ገልፀዋል።