“የሚላስ የሚቀመስ የለንም” ያሉ የቡሬ ወረዳ የጥቃት ተፈናቃዮች ለአስቸኳይ ድጋፍ ተማፀኑ

Your browser doesn’t support HTML5

“የሚላስ የሚቀመስ የለንም” ያሉ የቡሬ ወረዳ የጥቃት ተፈናቃዮች ለአስቸኳይ ድጋፍ ተማፀኑ

ከዐማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ወረዳ፣ በጸጥታ ችግር ሳቢያ ተፈናቅለው፣ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ውስጥ የሚገኙ ዜጎች፣ በቂ ድጋፍ እንዳላገኙና ለችግር እንደተጋለጡ አስታውቀዋል።

አስተያየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ የሰጡ ተፈናቃዮች፣ መንግሥት በአስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

የወረዳው ቡሳ ጎኖፋ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ተወካይ አቶ መኰንን ተረፈ፣ ከቡሬ ወረዳ ከ3ሺሕ800 በላይ ዜጎች እንደተፈናቀሉና በሁለት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልጸው፣ የመንግሥት ድጋፍ በቂ እንዳልኾነ አመልክተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።