በአሜሪካ ለሄሪኬን ተጎጂዎች ሰለባዎች ተጨማሪ እርዳታ እየቀረበ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

በአሜሪካ ለሄሪኬን ተጎጂዎች ሰለባዎች ተጨማሪ እርዳታ እየቀረበ ነው

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በከባዱ ዝናባማ አውሎ ንፋስ ሄሪኬን ሚልተን ቀደም ብሎም በሄሪኬን ሂለን የተጎዱ የፊሎሪዳ አካባቢዎችን ትላንት ዕሁድ ጎብኝተዋል፡፡ በዚሁ ወቅትም የአካባቢውን የኢሌክትሪክ ኃይል ማሰራጫ ዓቅም ለማጠናከር የሚውል ግማሽ ቢሊዮን ዶላር አዲስ ድጋፍ መመደቡንም ይፋ አድርገዋል፡፡ የእርዳታ እና የመልሶ ማቋቋም ጥረቶቹ ቀጥለዋል፡፡ ባለስልጣናት ታዲያ የፕሬዚደንታዊ ምርጫው ቀን እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት የሐሰት መረጃውም በተፋጠነ ሁኔታ እየተዛመተ መሆኑን በማመልከት ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ፓትሪክ ብሬዝናን ከሰሜን ካሮላይና ያጠናቀረውን ዘገባ ቬሮኒካ ኢግሊሲያስ ባልዴራስ አቅርባዋለች፡፡ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡