በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ላይ የሚካሄድ ከፍተኛ ስብሰባ ዋሽንግተን ላይ በፕሬዚዳንት ኦባማ ተጠርቷል፡፡
የስምንቱ የዓለም ከበርቴ ሃገሮች (G8) መሪዎች ስለአፍሪቃ የምግብ ዋስትና ለመወያየት በሣምንቱ መጨረሻ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ በሚገኘው ተራራማው የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች ማረፊያ፣ ካምፕ ዴቪድ ሊገናኙ ነው።
ሆኖም የወቅቱ የአውሮፓ ኢኮኖሚ ሁኔታ የተሰብሳቢዎቹን ትኩረት ሊስብ እንደሚችል እየተሰማ ነው፡፡ የአውሮፓ ዕዳ ቀውስና ቀውሱ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው አንድምታ የባሰ ሳያሳስባቸው አይቀርም።
ለመጀመሪያ ጊዜ በ ጂ8 ጉባዔ ከሚካፈሉ መሪዎች መካከል የፈረንሣዩ አዲስ ፕሬዚደንት ፍራንሷ ኦላንድ አንዱ ሲሆኑ ከመሪዎቹ ጉባዔ በፊት በዋይት ሃውስ ተገኝተው ከፕሬዚደንት ኦባማ ጋር ይወያያሉ።
ሚስተር ኦላንድ የቀበቶ አጥብቁ ፖሊሲአቸው ያላስደሰተው የፈረንሣይ ህዝብ በምርጫው ከሥልጣን ያነሳቸውን ኒኮላስ ሣርኮዚን የተኩ መሆናቸው ይታወቃል።
ብዙ ተንታኞች የ G8 ከበርቴ አገሮች መሪዎች የአውሮፓ ኢኮኖሚ ፖሊሲ አቅጣጫ እንዲቀየር አይፈቅዱም የሚል አስተያየት ይሰጣሉ።
ሆኖም የግሪክ የዩሮ ተጠቃሚ አገሮች አባል መሆን በአውሮፓ ኢኮኖሚ ላይ የባሰ አደጋ ያጠላል የሚሉ ተንታኞችና ባለሙያዎች ይደመጣሉ፡፡
ዝርዝሩን ከዘገባው አዳምጡ፡፡