የሃይማኖት አባቶች በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት ጉዳይ እንዳሳሰባቸው ተናገሩ

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት የምንኩስና ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መገደዳቸውን በተመለከተ ለፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ እስር ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥ ታዟል።

Your browser doesn’t support HTML5

የሃይማኖት አባቶች በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት ጉዳይ እንዳሳሰባቸው ተናገሩ

በሌላ በኩል በውጭ የሚኖሩ የኃይማኖት አባቶች በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት ጉዳይ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። በተለይ የመነኮሳት ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መጠየቃቸው ለፍርድ ቤት መናገራቸውን አንስተው “አንድን መነኩሴ ቀኖናችሁን አፍርሱ ማለት አይቻልም” ብለዋል።

በተያያዘ የፌደራል ዐቃቤ ሕግ በክርክር ሂደት ላይ የነበሩትን የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች ክስ ሲያቋርጥ በተፈጠረው የስም መቀያየት ምክኒያት አንዱ ተከሳሽ አጥናፉ ብርሃኔ መከላከያ ምስክሮቹን አቅርቦ ሒደቱ እንዲቀጥል ተብሏል።