ዋልድባ ገዳምና የስኳር ፕሮጀክት

ዋልድባ ገዳም በሚገኝበት አካባቢ ይካሄዳል የተባለን የስኳር ልማት አስመልክቶ ውዝግብ ተነስቷል፡፡

የዋልድባ ገዳም ይዞታዎች የሆኑ አካባቢዎችን «መንግሥት ለልማት ሊያውል ነው፤ በተለይም የስኳር ፋብሪካ ሊያቋቁምበት ነው» የሚል መረጃ ስለደረሰን ሁኔታውን ለማጣራት ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሰዎች ከቦታው አጋግረናል።

በዚሁ መሠረት ሁለት ፕሮግራሞችን ስናቀርብ የመንግሥትን ወገን አላገኘንም ነበር።

ባለፈው ረቡዕ ግን ከዚያው ከአካባቢው የማይፀብሪ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሣይ መረሳ መልስ ሰጡንና የሁለት አባቶችን አስተያየት አካትተን አቅርበነዋል።

በዚህ ዝግጅት ባለፈው ረቡዕ የላለፈውን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢው አዲሱ አበበ ከአንዳንድ ተጨማሪ ማብራሪያዎች ጋር አጣምሮታል።

ያዳምጡት፡፡