የአገው ታጣቂ ቡድን እና የክልሉ መንግሥት የሰላም ስምምነት

Your browser doesn’t support HTML5

የአገው ታጣቂ ቡድን እና የክልሉ መንግሥት የሰላም ስምምነት

በአማራ ክልል በዋግ ህምራ ዞን በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ሲንቀሳቀስ በነበረው" ራሱን የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ " በማለት በሚጠራው ታጣቂ ቡድንና በክልሉ መንግስት መካከል በቅርቡ የሰላም ስምምነት መፈረሙን ሁለቱም ወገኖች አስታውቀዋል።

ላለፉት ሦስት ዓመታት በዞኑ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ 16 ቀበሌዎች የትጥቅ ትግል ሲያደርግ ከነበረው ቡድን ጋር የተደረሰው ስምምነት “በአካባቢዎቹ የሚኖረውን እና በጸጥታ ችግር ምክንያት መሠረታዊ አገልግሎት የማያገኘውን ሕዝብ ለመታደግ ያስችላል” ሲሉ ሁለቱም ወገኖች ተናግረዋል።

የሰላም ስምምነቱ በአዲስ አበባ ከተማ የተፈረመው ታህሳስ 13/2016 ዓ.ም መሆኑንና ባለፈው እሁድ ታህሳስ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ ፣ለዞኑ ሕዝብ ይፋ መደረጉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሀይሉ ግርማይ ገልፀዋል።

ታጣቂ ቡድኑ ተቆጣጥሯቸው በቆዩት፣ ፃግብዥና አበርገሌ ወረዳዎች ውስጥ ባለፉት ሶስት አመታት፣ከ30 ሺ በላይ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውንም ዋና አስተዳዳሪው አክለው አመልክተዋል::

ራሱን" የአገው ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ " ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ሊቀ መንበር መሆናቸውን የገለፁልን አቶ ኪሮስ ሮምሃ በበኩላቸው የሰላም ስምምነቱ ዋነኛ ምክንያትና ዓላማ ታጥቀው በሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ያለው የዋግ ህዝብ ለከፋ ረኀብ መዳረጉና እንደ ትምህርትና ጤና ያሉ ማህበራዊ ግልጋሎቶችን አለማግኘቱ ያስከተለውን ስቃይ መቀነስ እንደሆነ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያድምጡ፡፡