በዋግኽምራ ዞን 15 ሕፃናት በኩፍኝ ወረርሽኝ ሕይወታቸው ማለፉን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ

የኢትዮጵያ

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መደበኛ ክትባት በመቋረጡ በተከሠተው የኩፍኝ ወረርሽ፣ ባለፈው ወር ብቻ 15 ሕፃናት መሞታቸውን፣ የዞኑ ጤና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

Your browser doesn’t support HTML5

በዋግኽምራ ዞን 15 ሕፃናት በኩፍኝ ወረርሽኝ ሕይወታቸው ማለፉን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ፣ ዛሬ ማክሰኞ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ በአካባቢው በተደጋጋሚ ባጋጠመው የጸጥታ ችግር የተነሣ ሕፃናት በዕድሜያቸው ማግኘት የነበረባቸውን መደበኛ ክትባት አላገኙም።

ከአምስት ወራት በፊት በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ብቻ ተከሥቶ የነበረው የኩፍኝ ወረርሽኝ በኹሉም ወረዳዎች በመስፋፋቱ፣ በአሁኑ ሰዓት ሁለት ሺሕ ሕፃናት በወረርሽኙ መያዛቸውን ገልጸዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

የሰሜን ወሎ፣ አጎራባች ዞንና ክልሎች ተፈናቃዮች በደሴ

በቅርቡ፣ ለሕፃናቱ በዘመቻ መልክ የክትባት አገልግሎት እንደሚጀመር የጠቆሙት ኃላፊው፣ በጸጥታው ችግር የተነሣ ለባለሞያዎች ተደራሽነት አዳጋች በኾኑ ወረዳዎች ያሉ ሕፃናትን ለመታደግም ረጂ ድርጅቶች ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡