በሺሕዎች የሚቆጠሩ የቤት እንስሳትን በከባድ ድርቅ ያጡ የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ነዋሪዎች “ቀጣይ ኑራችን ተስፋ የለውም” አሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በሺሕዎች የሚቆጠሩ የቤት እንስሳትን በከባድ ድርቅ ያጡ የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ነዋሪዎች “ቀጣይ ኑራችን ተስፋ የለውም” አሉ

በዐማራ ክልል በዋግ ኽምራ ዞን በሰሀላ ሰየምት ወረዳ፣ በ2015/16 የመኸር ምርት ዘመን የተከሠተው የዝናም እጥረት ባስከተለው ከባድ ድርቅ፣ ከአራት ሺሕ በላይ የቤት እንስሳት እንደሞቱና በሚሊዮን የሚቆጠሩትም ወደ አጎራባች አካባቢዎች እየተሰደዱ እንደኾኑ ተገለጸ፡፡

የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሓላፊ አቶ ምሕረት መላኩ፣ ዛሬ ረቡዕ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ከ22 ግብረ ሠናይ ድርጅቶች እና ከመንግሥታዊ ተቋማት ተወጣጥቶ የተቋቋመው የጥናት ቡድን ወደ ወረዳው አምርቶ፣ ድርቁ ያስከተለው ችግር ከፍተኛ እንደኾነ አረጋግጧል፡፡

ያነጋገርናቸው የሰሀላ ሰየምት ወረዳ ምሽሀ ቀበሌ አርሶ አደሮችም፣ የቤት እንስሶቻቸው በመሞታቸው ለፈታኝ ሕይወት እንደተዳረጉ አመልክተዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡