በዋግ ኽምራ ዞን ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ

Your browser doesn’t support HTML5

በዋግ ኽምራ ዞን ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ

በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን፣ ከ2016 ዓ.ም የመኸር ወቅት ጀምሮ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ምክኒያት ከ200 ሺሕ በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የዞኑ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ምሕረት መላከ፣ ባለፈው ክረምት በዞኑ ደጋማ አካባቢዎች የደረሰውን የተፈጥሮ አደጋ ተከትሎ ከ14 በላይ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች በአደረጉት ግምገማ 44 ሰዎች መሞታቸውን ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።