የባሕር ሞገድ ቀዛፊው የፊልም ባለሞያ

Your browser doesn’t support HTML5

የባሕር ሞገድ ቀዛፊው የፊልም ባለሞያ

ዴቪድ መስፍን፣ ነዋሪነቱን በካሊፎርኒያ ግዛት ያደረገ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የማስታወቂያ እና የፊልም ባለሞያ ነው። በሌላ በኩልም፣ የባሕር ሞገድን ይቀዝፋል።

በመደበኛ መጠሪያው ዳዊት፣ በዩናይትድ ስቴትስ ስፖርት ታሪክ ከፍተኛ ትኩረት ለሚሰጠው የአሜሪካ ሱፐር ቦል ማስታወቂያ ለአምስት ጊዜ በመሥራት አሸናፊ ኾኗል።

በተጨማሪም ‘ዌድ ኢን ዘ ዋተር’ የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም ሠርቷል። የአንድ ሺሕ ዘመን የአፍሪካ አሜሪካውያንን የዋና እና የባሕር ላይ ሞገድ ቀዘፋ ታሪክ የሚቃኘው ዘጋቢ ፊልሙ፥ ከ10 በላይ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችንና እውቅናዎችን አግኝቷል።