የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ በመሬት ጉዳይ አዲስ የህገ መንግሥት ማሻሻያ አፀደቀ

  • ቪኦኤ ዜና

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ

የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ መሬት ካለካሳ መውረስ በሚያስችል መልኩ የረቀቀ የህገ መንግሥት ማሻሻያ አፀደቀ።

የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ መሬት ካለካሳ መውረስ በሚያስችል መልኩ የረቀቀ የህገ መንግሥት ማሻሻያ አፀደቀ።

ርምጃው የሚበዛው የእርሻ መሬት አሁንም በኅዳጣን ነጮች እጅ በሚገኝባት ሀገር ይህ ፓርላማው የወሰደው ርምጃ ከባድ ጉዳይ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ሆኖም የዚህ የህገ መንግሥት ማሻሻያ ርምጃ ዋናው አስተባባሪ በማሻሻያው ምክንያት የሚመጣ ከባድ ርምጃ እንደሌለ በመግለፁ ሕዝቡን ሊያረጋጉ ሞክረዋል።

አክራሪ የሆነው የኢኮኖሚ ነፃነት ተዋጊዎች ፓርቲ መሪው ጁሊየስ ማሌማ ቤቱን ወይም ፋብሪካውን ወይም ኢንዱስትሪውን ማንም አይነጠቅም።

የመሬት ባለቤትነት ይቀርና በሊዝ ይከራያል። ይሄ ደግሞ በሕገ መንግሥታዊ ግምገማው ሂደት የሚወሰን ይሆናል ብለዋል።

ይህ የፓርላማው ርምጃ ደቡብ አፍሪካን እንደጎረቤትዋ ዚምባቡዌ ያደርጋታል የሚል ሥጋት አለ።