የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች፥ አዲሱ ሰባት ኪሎ መጽሔት፥ እና ሌሎች ሙዚቃ ነክ ወጎችና የሃሳብ መስመሮች፤

Amharic Radio Magazine Program Banner

“ሰባት ኪሎ” የሚል ሥያሜ ስለ ሰጡትና በቅርቡ ለንባብ ስለ በቃው መጽሔታቸው፥ ጋዜጠኝነት በስደትና መንገዶቹ የሚያወጉን እንግዶች፤ ከቀድሞዎቹ አዲስ-ነገሮች ሁለቱ ለራዲዮ መጽሔት ወግ ተሰይመዋል።

ከዓመታት በፊት “መርካቶ ሰፈሬ፤” በተሰኘችው ዜማው ከሙዚቃ አድናቂዎች ጋር የተዋወቀው ድምጻዊ አብዱ ኪያር “ጥቁር አንበሳ” በሚል ሥም ያወጣውን አዲስ አልበም ይዞ ብቅ ብሏል።

በእንግሊዥናው ምሕጻረ ቃል AFRIMA በመባል ለሚታወቀው “የመላው አፍሪቃ ዓመታዊ የሙዚቃ ሽልማት” ለሁለተኛ ጋዜ ከተመረጠችው ድምጻዊት ጸደኒያ ገብረማርቆስ ስለ ሽልማቷ፥ የውድድሩ ሂደትና ሌሎች ተዛማች ርዕሶች እንነጋገራለን።

“የሃሳብ መስመር” ... የተለያዩ ጉዳዮችንና ሁኔታዎችን የሚመለከቱ ጭብጦች መናሃሪያ ነው። እውነት ምንድ ናት? በሚል ጥያቄ ዙሪያ ያጠነጥናል።

ሕዳር ይታጠናል። የዕለቱ የታሪክ ማስታወሻ ከአዲስ አበባ ተቀናብሯል።

የሳምንቱን የራዲዮ መፅሔት ወጎች እነሆ፤

Your browser doesn’t support HTML5

የሳምንቱ የራዲዮ መፅሔት ወጎች “ቅምሻ”

Your browser doesn’t support HTML5

“ኑዛዜ፤” - የሳምንቱ ምርጥ ግጥም፤ በሰለሞን ሞገስ፤

Your browser doesn’t support HTML5

ከድሞዎቹ የአዲስ-ነገሮች፤ ከሁለቱ የአዲሱ “ሰባት ኪሎ” መጽሔት አዘጋጆች ጋር (የመጀመሪያ ክፍል)

Your browser doesn’t support HTML5

የሙዚቃ ወጎች፤ i) የአብዱ ኪያር “የኔ ማር” እና ሌሎች የሙዚቃ ነክ ጉዳዮች፤

Your browser doesn’t support HTML5

ii) ጸደኒያ ገብረማርቆስ እና የARIMA 2015 ሽልማቷ፤

Your browser doesn’t support HTML5

“ሕዳር ሲታጠን” እና ሌሎች የታሪክ ማስታወሻዎች፤

Your browser doesn’t support HTML5

“የሃሳብ መስመሮች” ... መነጋገሪያ ”እውነት ምንድ ናት?” .. እንደ ማስታዋወቂያ