ከኮምሽነር ዳንኤል በቀለ ጋራ የተደረገ ቃለ ምልልስ

Your browser doesn’t support HTML5

ከኮምሽነር ዳንኤል በቀለ ጋራ የተደረገ ቃለ ምልልስ

በጦርነቱ ወቅት ትግራይ ውስጥ “ተፈጽመዋል” የተባሉት የሰብዓዊ መብት ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎችን፣ የስብዕና እና የስደተኛ ሕግጋት መጣስ ሲያጣራ የቆየው ጥምር መርማሪ ቡድን ዛሬ ባወጣው የግኝቱ ሪፖርት የጦር ወንጀሎች እና በስብዕና ላይ የተፈጸሙ ሊባሉ የሚችሉ ወንጀሎች በሁሉም ወገኖች ስለመፈጸማቸው አሳማኝ መሰረቶች አሉ ብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮምሽነር እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮምሽን በጋራ ያካሄዷቸውን ምርመራዎች ዛሬ ማለዳ ላይ ጄኔቭ እና አዲስ አበባ ላይ ባቀረቡት ሥነ ሥርዓት ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከማብራሪያው በኋላ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮምሽነር ዳንኤል በቀለ በተለይ ከአሜሪካ ድምጽ ቃለ ምልልስ አካሂደዋል።