ዓርብ፤ ነኀሴ 13/2008 ዓ.ም ችሎት ፊት ይቀርባሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ከወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ መሪዎች አንድ የሆኑት ኮሎሌል ደመቀ ዘውዴ ለሁለተኛ ጊዜ ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡
በዕለቱ ፖሊስ ተከሣሹን ያላቀረበበት ምክንያት በግልፅ ባይነገርም አንዳንድ ነዋሪዎች ግን የሚመስሏቸውን ሃሣቦች ለቪኦኤ ጠቁመዋል፡፡
የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ዋና ፀሐፊና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው የሆኑት አቶ ተሻገር ወልደሚካኤል ኮሎኔል ደመቀን ሰሞኑን እሥር ቤት ሄደው እንዳገኟቸውና እንደተወያዩ ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተለያዩ ሃሣቦች የተንፀባረቁበት ውይይት በቪኦኤ ተካሂዷል፡፡
ኢትዮጵያ አስከፊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ መግባቷን በመጥቀስ ከቀውሱ ለመውጣት ኢሕአዴግ ከሥልጣን ወርዶ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም የሚጠይቁ ወገኖች አሉ።
ተፈጥሯል በሚሉት ቀውስ ተስማምተው የሽግግር መንግሥት መቋቋምን ሃሣብ የሚነቅፉም አሉ።
የሕወሐት የቀድሞ ታጋይ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ከጄኔቭ፣ የጋራ እንቅስቃሴ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ ከዋሽንግተን ዲሲ፣ የቀደሞ የፓርላማ አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ከአዲስ አበባ እንዲሁም በትግርኛ ቋንቋ የሚታተመው “ውራይና” መፅሔት አዘጋጅ አቶ ጌታቸው አረጋዊ ከአዲስ አበባ በጉዳዩ ዙርያ ያላቸውን ሐሳብ ለአሜሪካ ድምፅ ሰጥተዋል።
ሙሉ ዘገባዎችን ከተያያዘው የእሁድ ዝግጅት የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5