የክራሯ ንግሥት አስኒ ስትታወስ

Your browser doesn’t support HTML5

በቀደመው ዘመን፣ በዳንስ እና ውዝዋዜ፣ በልዩ ዝነጣ፣ እንዲሁም በክራር በታጀበ ሙዚቃዋ ነግሣ ኖራለች። በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የመድረክ ተዋናይትም ናት፤ አስናቀች ወርቁ። በዕድሜ ዘመንዋ መካተቻ ላይ ፣ እርሷን የሚዘክር “አስኒ” የተሰኘ ፊልም ተሠርቶ በቪሚዮ መተግበሪያ ላይ እየታየ ይገኛል። የ “አስኒ” ፊልም ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር ሬቸል ሳሙኤል፣ ፊልሙ እንዴት እንደተሠራ፣ እንዲሁም አስኒ ስለነበራት ሰብእና ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ ቆይታ አድርጋለች።