ግድያ ሲፈጸም ያሳያሉ በሚል የወጡት ያልተረጋገጡ ቪዲዮዎች በኢትዮጵያ ቁጣን ቀስቅሰዋል

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ተገድሏል የተባለውን ወጣት በተመለከተ የፌደራልና የክልል መንግሥት ባለሥልጣናት “ኾን ተብሎ የተፈጸመ የጭካኔ ድርጊት" በማለት ከትላንት በስተያ ሐሙስ ዕለት አጥብቀው አውግዘዋል። የፌደራልና የክልል ባለሥልጣናት ውግዘት የመጣው፣ ሁለት የማሰቃየት እና “አንገት የማረድ” አድራጎት ሲፈጸም ያሳያሉ የተባሉ ያልተረጋገጡ የቪዲዮ ክሊፖች በማኅበራዊ ድህረ ገጾች መሰራጨታቸውን ተከትሎ ነው።