በልደት ቀኗ የልብ ሕሙማንህፃናትን የምትጠግነው

Your browser doesn’t support HTML5

ሕይወት ታደሰ የምትኖረው ዩናይትድ ስቴትስ ነው። በየዓመቱ በልደት ቀኗ የተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕፃናት ገንዘብ ትለግሳለች። ሕይወት ዘንድሮ 1.2 ሚሊየን ብር አሰባስባለች። ይሄ ተግባሯ የባንክ ሂሳቧን እስከመዘጋት የሚያደርስ ፈተና ላይ ቢያደርሳትምአንዴ ተነሳስታ ቆርጣለችና “ላይፍ ፎር አፍሪካ” ብላ የሰየመችውን ድርጅት መሠረተች። ሥራዋን ለጋቢና ቪኦኤ አድማጮች አካፍላለች። /ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ/