የአማረኛ ቋንቋ ሥርጭትን ከጀመሩት ጋዜጠኞች ሦስቱን ቃለ መጠይቅ አድርገንላቸዋል፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
ጥቅምት 15/1975ዓ.ም ልክ የዛሬ 35 ዓመት የመጀመሪያውን ሥርጭቱን ለዓየር ያበቃው የአሜሪካ ድምጽ የክፍሉን ኃላፊ እና የፕሮግራም አቀናባሪውን ጨምሮ ስምንት አባላት ነበሩት።
ከመጀመሪያዎቹ የክፍሉ ባልደረቦች ሦስቱ አሁንም በጣቢያው በተለያዩ ክፍሎች በማገልገል ላይ ናቸው።
ንጉሴ መንገሻ አሁን የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር ነው።
አዳነች ፍስሃዬ በአማርኛው ክፍል በማገልገል ላይ ትገኛለች።
ይሄይስ ውሂብ በእንግሊዝኛው ክፍል ይሠራል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ከፍተው ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5