የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት አሞገሱ

የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ገለጹ። አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎችም እርዳታውን እያገኙ ናቸው ብለዋል።

የ USAID ማለትም የ United States አለም አቀፍ ተራድኦ ከፍተኛ ምክትል አስተዳዳሪ Gregory Gotlied በኢትዮጵያ ስላለው የድርቅ ሁኔታ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣

“በኢትዮጵያ ረሃብ የለም እንላለን። አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በሱማልያያለውን አይመስልም። ያ ረሃብ ነው። የእነሱ በተመጣጠነ ምግብ እጦት ከሚታይ ጉዳት በላይ ነው። እዚህ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ አይነት ሁኔታ የለም። እና በዚያ ረገድ እዚህ ይሻላል።" ሲሉ አብራርተውታል።

በኢትዮጵያ በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተጎዱ ህጻናት ክሊኒክ ሄደው ተገቢውን ህክምና ያገኛሉ። ከምግብ ዋስትና አኳያም የምናያቸውና ተስፋ የምናደርግባቸው አዝማምያዎች አሉ በማለት Gregory Gotlied አብራርተዋል።