ዩኤስኤይድ እና ሌጎ ፋውንዴሽን የኢትዮጵያ ህፃናት እንክብካቤ እና ትምህርት ለማሻሻል በጋራ ሊሰሩ ነው

ከዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

ከዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት እና ሌጎ ፋውንዴሽን የተባለው ህፃናትን በትምህርት በፈጠራ አቅም ለማሳደግ ለማበረታት የሚሰራ የበጎ አድራጎት ተቋም በጋራ አዲስ መርኃ ግብር መወጠናቸውን አስታወቁ።

ሁለቱ ድርጅቶች በግጭቶች እና በቀውሶች በተጎዱ አካባቢዎች ያሉ በመዋዕለ ህፃናት ዕድሜ ክልሎች ውስጥ ባሉ ልጆች ላይ እየተጫወቱ እና እየተማሩ እንዲያድጉ ለማስቻል በጋራ ቢያንስ ሃያ አምስት ሚሊዮን ዶላር ወጪ አድርገው መርኃ ግብሮችን እንደሚያዘጋጁ ከዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የወጣው መግለጫ አመልክቷል።