ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለማቀፉን ሚዲያ ኤጂንሲ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ነፃና ገለልተኛ የሆነ ሚዲያ፣ በዓለም እንዲስፋፋ አርአያ የሚሆን ዘመናዊ የሚዲያ ተቋም እንዲኖር በዩናትድ ስቴትስ መንግሥት በጀት የተቋቋመው ኤጀንሲ ነው፡፡ ማይክ ፓክ በኮንግረስ የበላይ ጠባቂነት ሲተዳደር የኖረውን ይህን ኤጄንሲ እንዲመሩ፣ በተፈጠረ አዲስ መዋቅር፣ በፕሬዚዳንት የተሾሙ የመጀመሪያው ባለሥልጣን ናቸው፡፡
የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ /ቪኦኤን/ ጨምሮ፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ዓለማቀፍ ሚዲያ ኤጂንሲ ሥር የሚገኙ የዜና አውታሮችን ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በሥራ አስፈፃሚነት እየመሩ ያሉት ማይክ ፓክ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችን በማባረርና ለውጭ ሃገር ጋዜጠኞች የቪዛ እድሳቶችን በማቋረጥ በወሰዷቸው እርምጃዎች፣ ከፍተኛ ትችት ቀርቦባቸዋል፡፡
ከሁለቱም የዲሞክራቲክ እና የሪፖብሊካን የምክር ቤት አባላት ብርቱ ትችት ስለቀረበባቸው ሥራ አስፈፃሚው በምክር ቤቱ የቪኦኤ ዘጋቢ ካትሪን ጊብሰን ዘገባ ይዘናል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5