በዩናይትድ ስቴትስ ቬቴራንስ ዴይ እየተከበረ ነው

  • ቪኦኤ ዜና

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ቨርጂኒያ በሚገኘው በአርሊንግተን ብሂራዊ የአርበኞች መካነ መቃብር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል

በዩናይትድ ስቴትስ ቬቴራንስ ዴይ/የአርበኞች ቀን/ እየተከበረ ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይሎች ያገለገሉ አርበኞች የሚከበሩበት እና የሚታሰቡበት ቬቴራንስ ዴይ በሀገሪቱ ዙሪያ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እና ሰልፎች እየተከበረ ይገኛል።

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ቨርጂኒያ በሚገኘው በአርሊንግተን ብሂራዊ የአርበኞች መካነ መቃብር በተከናወነው የቬቴራንስ ዴይ እንዲሁም ያልታወቀው ወታደር መታሰቢያ ሀውልት አንድ መቶኛ ዓመት መታሰቢያ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

ባይደን ዋይት ሀውስን ከተረከቡ የመጀሪያቸው በሆነው በዚህ የአርበኞች ማክበሪያ ዕለት አስተዳደራቸው፣ በውጭ ሀገሮች በግዳጅ ላይ ሳሉ ለተመረዘ አየር ለተጋለጡ የጦር አርበኞች የተሻለ ህክምና እንዲሰጥ እንዲያደርጉ ተያያዥ ሊሆኑ በሚችሉ በሽታዎች ላይ ጥናት እንዲካሄድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።