ብሊንክን በዩክሬይንና በጋዛ ጦርነቶች ጉዳይ ወደ ፓሪስ እና ብራስልስ ይጓዛሉ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ብሊንክን በዩክሬይንና በጋዛ ጦርነቶች ጉዳይ ወደ ፓሪስ እና ብራስልስ ይጓዛሉ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ፈረንሳይ እና ወደ ቤልጂየም ይጓዛሉ።

ጉብኝታቸው፣ ለዩክሬይንና እስራኤል በሐማስ ታጣቂዎች ላይ ለምታካሒደው ጦርነት በሚሰጡት ድጋፍ ላይ፣ የዩናይትድ ስቴትስን የቅርብ አጋሮች አንድነት ለማጠናከር ያለመ ነው፤ ተብሏል።

ተንታኞች እንዳመለከቱት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ብርቱ ሥራ ይጠብቃቸዋል።

የቪኦኤ የዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ዋና ዘጋቢ ሲንዲ ሴን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።