ሶርያ ባሉ ኩርዶች ላይ የተከፈተ ጥቃት እንዲቆም ተጠየቀ

  • ቪኦኤ ዜና

የቱርክ ፕረዚዳንት ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋን እና የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕረዚዳንት ማይክ ፔንስ

የቱርክ ፕረዚዳንት ረጂፕ ታይፕ ኤርዶዋን በሰሜን ሶርያ ባሉት ኩርዶች ላይ የከፈቱትን ጥቃት እንዲያቆሙ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕረዚዳንት ማይክ ፔንስ ዛሬ ግፊት እያደረጉ ነው።

ኤርዶዋን ጥቃት የከፈቱት የዩናይትድ ስቴትስ ፐረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሞላ ጎደል ሁሉም የአሜሪካ ወታደሮች ከጦር ግንባሩ እንዲወጡ ካዘዙ በኋላ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ፔንስ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮና ከዋይት ሀውስ የብሄራዊ ጸጥታ ጉዳይ አማካሪ ሮበርት ኦብራያን ጋር ሆነው በቱርክ መዲና አንካራ ላይ ከሀገሪቱ መሪ ጋር ተነጋግረዋል።

ፕረዚዳንት ትራምፕ በሰሜን ምስራቅ ሶርያ የሚካሄደው ውጊያ “እኛን አይመልከትም ባሉበት ወቅት ነው ንግግሩ የተልካሄደው። የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአሜሪካ ወታደሮች ከጦር ሜዳው መውጣታቸውን በከፍተኛ ድምጽ አውግዟል።

ትራምፕ ግን እስላማዊ መንግስት ንኝ የሚለውን ጽንፈኝ ቡድን በመታገል ረገድ ከአሜሪካ ወታደሮች ጎን ሆነው የተዋጉትን ኩርዶች “ እነሱም ቢሆኑ መላእክት አይደሉም” ሲሉ ማጥላላታቸው ተዘግቧል።

ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ለኤርዶዋን የላኩት አጭር ደብዳቤ በኩርዶች ላይ ፍጅት ለመፈጸም “ጀግንነት አይሰማዎት። ቂል አይሁኑ” የሚል እንደነበርና ኤርዶዋን ደብዳቤውን በቁሻሻ ቅርጫት ላይ እንደጣሉት ተዘግቧል።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕረዚዳንት ጃን ክላውድ ጃንከር በበኩላቸው ዛሬ በትዊተር ባስተላለፉት መልእክት “ፋላጎት ካለ ስምምነት ይኖራል። ዛሬ አሸንፈናል” ብለዋል። ሁለቱም ወገኖች ከሶስት አመታ በላይ ለሆነ ጊዜ ሲነታረኩ ከቆይ በኋላ ነው ዛሪ ስምምነት ላይ ሊደርሱ ያቻሉት።

ስምምነቱ ለአውሮፕ ህብረትና ለብሪታንያ “ፍትሃዊና ሚዛናዊና ነው” ብለዋል ጃንከር። 27 ቱ የአውሮፓ ሀገሮች መሪዎች ዛሬ ብራሰልስ ሲሰባብሰቡ እንዲያጸድቱ ጥሪ አቅርበዋል።

ብሪታንያ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ከአውሮፓ ህብረት እንደምትወጣ ታውቋል።