የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ቱርክ በሰሜን ሶሪያ ያላትን እቅድ ተቃወሙ

ፎቶ ፋይል - የዩናይትድ ስቴትስ እና የቱርክ ኃይሎች ሶሪያ እና ቱርክ በሚያዋስነው ድንበር አካባቢ ቅኝት ሲይደርጉ፣ በሶሪያ ታል አብያድ አቅራቢያ እአአ መስከረም 8/2019

የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ቱርክ በሰሜን ሶሪያ በድጋሚ ልታካሂድ ያሰበችው ወታደራዊ ዘመቻ ያሳሰባቸው መሆኑን በይፋ እየገለጹ ነው፡፡

ባለሥልጣናቱ ይህ ዓይነቱ የቱርክ እምርጃ በአካባቢው ያሉ የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎችን ለአደጋ የሚያጋልጥና ከእስላማዊ መንግስት ተዋጊዎች ጋር በሚደረገው ትግል ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ ጥፋትና መዘዝ እንደሚያስከትል ገልጸዋል፡፡

ቱርክ ካላፈው ግንቦት ወር ጀምሮ በሶሪያ ድንበር በኩል አሁን ያለውን የ30 ኪሎ ሜትር የደህንነት ቀጠና ለማስፋት ሥጋት መደቀኗ ሶሪያ ውስጥ ባሉ የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች፣ በዋሽንግተንና በአንካራ መካከል ጠንከር ያለ ንግግር መቀስቀሱ ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ ንግግሮቹ ውጤት አለማምጣታቸውና ከአንካራ በኩል የሚሰሙ ዛቻዎች የተለያዩ የዩናይትድ ስቴት ባለሥልጣናት ወደ አደባባይ በመውጣት ከሌላው የቱርክ ወረራ ደህና ነገር ሊመጣ እንደማይችል እንዲገልጹ አድርጓቸዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ረዳት መከላከያ ሚኒስትር ዳና ስትራውል ዋሽንግተን ላይ በተካሄደ አንድ መድረክ “ቱርክ በሰሜን ሶሪያ ላይ የምታካሂደውን ማናቸውንም ወታደራዊ ዘመቻ አጥበቀን እንቃወማለን ይህንን ተቃውሟችንም ለቱርክ ግልጽ አድርገናል” ብለዋል፡፡

ረዳት ሚኒስትሯ አክለውም “ከዚያ ዘመቻ ተጠቃሚ የሚሆነው አይሲስ ነው” ማለታቸው ተመልክቷል፡፡

"ቱርክ በሶሪያና ኢራቅ ውስጥ የሚገኙ የተቃዋሚው ፒኬኬ እንቅስቃሴዎችን አስመልከቶ ስላላት ሥጋት ትገነዘባለች" ያሉት ረዳት ሚኒስትሯ “እነዚያን እንቅስቃሴዎችን በመቋቋም ፔንታገን ከቱርክ ጋር አብሮ መስራቱን ይቀጥልበታል ሲሉ” ቃል ገብተዋል፡፡

ይሁን እንጂ የቱርክ ወረራ እጅግ ርቆ የሄደ እምርጃ ነው ሲሉ ባለሥልጣኗ አስጠንቅቀዋል፡፡