ወደዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ ለሚፈልጉ የቱርክ ዜጎች ሙሉ የቪዛ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር በሀገሪቱ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
ዋሺንግተን ዲሲ —
ወደዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ ለሚፈልጉ የቱርክ ዜጎች ሙሉ የቪዛ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር በሀገሪቱ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
በዚሁ የአውሮፓውያን ዓመት ውስጥ ኢስታንቡል የሚገኘው ቆንስላዋ ሠራተኛ ሜቲን ቱፖዝ በሽብርተኝነት ክስ መታሰሩን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ለጉብኝት ለሥራ ጉዳይ ወዘተ ለመግባት ለሚፈልጉ በሙሉ ቪዛ አገልግሎት አቁማ እንደነበር ይታወሳል።
ቱርክም በአፀፋው በዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲዋ የቪዛ አገልግሎት አቋርጣ ቆይታለች።