ዩናይትድ ስቴትስና ሱዳን ከ20 ዓመታት በኋላ አምባሳደሮች ሊለዋወጡ ነው

  • ቪኦኤ ዜና
የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ

ዩናይትድ ስቴትስ እና ሱዳን ከሀያ በሚበልጡ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አምባሳደሮች እንደሚለዋወጡ ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ አስታወቁ።

ይፋ የሆነው የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ የመጀመሪያቸው ለሆነው ጉብኝት ዋሺንግተን በገቡበት ወቅት ነው።

ይህ ውሳኔ በተለይም በሲቪል የሚመራው የሽግግር መንግሥት በስፋት የለውጥ ዕርምጃዎችን እየወሰደ ባለበት በዚህ ወቅት የሃገሮቻችንን ግንኙነት ለማጠናከር ትልቅ ዕርምጃ ነው ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፖምፔዎ፡፡