የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር አስተዳደር የርስ በርስ ጦርነቱን ለማስቆም የተደረሰውን ሥምምነት ተግባራዊ የማያደርግ ከሆነ ዩናይትድ ስቴትስ ተጨማሪ ማዕቀቦች ለመጣል ዝግጁ ነች ሲሉ በደቡብ ሱዳን የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ቶማስ ሀሼክ አስታወቁ።
ዋሺንግተን ዲሲ —
አምባሳደሩ ትናንት ጁባ ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል የሀገሪቱ መሪዎች የሰላም ውሉን ተግባራዊ ማድረግ ላይ ማትኮር አለባቸው ያ ካልሆነ ግን ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀቦቹን ልታጠናክር ትችላለች ብለዋል።
አምባሳደሩ “ተቃዋሚው መሪ ሪያክ ማቻር ተገኙም አልተገኙ የአንድነት መንግሥቱ በተያዘለት የኅዳር ወር የጊዜ ገደም ይቋቋማል” ሲሉ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በቅርቡ ላወጡት መግለጫ የሰጡት የቁጣ ምላሽ፡፡
እኛ ስለኅዳር 12 ስናስብ ተገኙም፣ አልተገኙ አንልም በኛ አመለካከት ኅዳር አሥራ ሁለት በሰላም ሥምምነቱ መሰረት ሁሉም ወገኖች የሚሳተፉበት የአንድነት መንግሥት ተግባራዊ የሚሆንበት የጊዜ ገደብ ነው። ሌላኛው ወገን በሌለበት በሰላም ሥምምነቱ መሰረት የተቋቋመ የአንድነት መንግሥት አይኖርም ብለዋል።