የዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀብ በሱዳን ላይ

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ በካርቱም ተቃዋሚዎች ወታደራዊ አገዛዝን በመቃወም የወጡት ሰልፍ እአአ ጥር 24/2022

ዩናይትድ ስቴትስ በሱዳን ሲካሄድ በቆየው የተቃውሞ እንስቃሴ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ረገጣ የሱዳን ማዕከላዊ ፖሊስ(ሴንተራል ሪዘርቭ ሴንተር) የተባለውን ኃይልን በጥፋተኝነት በመሰየም ማዕቀብ መጣሏን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን አስታወቁ፡፡

ብሊንክን በመግለጫቸው እምርጃው የተወሰደው በሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ግልበጣውን ተቃውሞ በወጡ ሰልፈኞች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥቃት የፈጸሙትን ሰዎች ተጠያቂ ለማድረግና ወደፊት ከሚፈጸሙ ጥቃቶች ለመከላከል ነው ብለዋል፡፡

ማዕቀቡ የተጣለው የሱዳን ኃይል በበርካታ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ተሳታፊ በሆኑ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ በተፈጸመው ጥቃት የተሳፊ በሆነው ተጠባባቂው ማዕከላዊ ፖሊስ የተባለው ወታደራዊው አካል ላይ መሆኑንም መግለጫው አመልከቷል፡፡

በተለይ እኤአ ጥር 7 በተደረገው ተቃሞው እነዚህ የተጠቀሱት ኃይሎች በተቃውሞ ሰልፎቹ ላይ በከፈቱት ተኩስ በርካታዎች መሞታቸውና መቁሰላቸውን መግለጫው አስታውቋል፡፡

ይህ እኤአ ጥምቅት 25/ 2021 ከተደረገው ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ወዲህ በተካሄዱ ተቃውሞ ሰልፎች ከተፈጸሙት ጥቃቶችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አንዱ መሆኑንም መግለጫው ጠቅሷል፡፡

አስገድዶ መድፈር፣ ግድያ፣ ማሰቃየት እና በዘፈቀደ ማሰር በማዕከላዊ ተጠባባቂ የፖሊስ ኃይሉ እኤአ እስከ መጋቢት 14 ድረስ ከተፈጸሙ ጥቃቶች መካከል ጥቂቆቹ ናቸው ብሏል፡፡

በተለይም እኤአ ታህሳስ 21 እና 22 እንዲሁም መጋቢት 14 በሴቶቹ የተቃዋሚ ሰልፈኞ ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ነው ብሏል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ የተባበሩት መንግስታት ለሚያደርገው ዘርፈ ብዙና የተቀናጀ የሽግግር ተልዕኮ ጥረት፣ የአፍሪካ ህብረትና የልማት በይነ መንግሥታት በሱዳናውያን የሚመራ የፖለቲካ ሂደት እንዲካሄድ በማድረግ ወደ ዴሞክራሲ የሚያመራ የሲቪል መር የፖለቲካ ሽግግር እንዲኖር የሚደረገውን ጥረት ዩናይትድ ስቴትት ሙሉ ድጋፏን ትሰጣለች ብሏል፡፡

የዛሬው እርምጃ ዩናትድ ስቴትስ በሱዳን ሁከትና ጥቃትን ለማቆምና የሱዳንን ሰላማዊ ሽግግር ወደ ቦታው ለመመለስ የምትችለውን ሁሉ የምታደርግ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡