በዓለም ላይ በሰፈነዉ የስደተኞች ቀዉስ ምክንያት የአሜርካ መንግስት ባለፈው ዓመት ብቻ 800 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ እርዳታ ለተለያዩ የስደተኞች መርጂያ ተቋማት መስጠቱን በአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የስደተኞች ክፍል ምክትል ጸሃፊ ካትሪን ዌይነር አስታወቁ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የአሜሪካ (United state) ምክር ቤት ተጨማሪ ወጪ ከመደበም ሰብአዊ እርዳታዉ በሚመጣዉ ዓመት ከፍ እንደሚል ጨምረዉ አስታዉቀዋል።
በአሁኑ ጊዜ የአፍሪቃ ስደተኞች ሁኔታ ከሌሎች በዓለም ላይ ከተከሰቱት የስደተኞች ቀዉስ ጋር ሲነጻጸር የአፍሪቃ ስደተኞች ሁኔታ እድግ የከፋ ነዉ ብለዋል የአሜሪካ ዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የስደተኞች ክፍል ምክትል ጸሃፊ ካትሪን ዌይነር። የአፍሪቃዊያን ስደተኞች ቁጥር 4.8 ሚሊዮን ሲሆን በያገሮቻቸዉ ከቤት ንብረተፈናቅለዉ የሚገኙ ደግሞ 12 ሚኢሎን እንደሚደርሱ ይህ ደግሞ የስብአዊ እርዳታ እጥረት ማባባሱን ተናግረዋል። ባለስልጣንዋ የአፍሪቃ 54 የቴሌቭዥን ፕሮግራም ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ጨምቀን እናቀርባለን።
የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5