የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ በኢትዮጵያ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን

"ዩናይትድ ስቴትስ የያዘቻቸው አንዳንድ አቋሞች ህወሓት በሕገወጥ ድርጊቱ እንዲገፋ የሚያበረታቱ ናቸው" ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ወቀሳ አሰምቷል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ኢትዮጵያ ከሚገኙት ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና አንድነት ቁርጠኛ አቋም እንዳላት አምባሳደር ጄፍሪ ፌልትማን መግለፃቸውንና አሁን ያለው ቀውስ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ወደ ቱርክ ሄደዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ በኢትዮጵያ